ማስታወቂያ
* ማስታወቂያ*
ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር አባላት!
የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ከመጪው ሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል በመንግሥት የተወሰነውን የኤሌክትሮኒክ ግዥ ሥርዓት የተመለከተ የውይይት መርኃ-ግብር አዘጋጅቷል፡፡
በዚሁ መሠረት በመጪው ሰኔ 13 ቀን 2015 ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል በሚዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በዚህ የግዥ ሥርዓት የተመዘገባችሁ አባላትም ሆናችሁ ያልተመዘገባችሁት የማኅበራችን አባላት እንዲሁም መላው የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች በዚሁ የውይይት መርኃ-ግብር ላይ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡
በተለይ በዚህ በአዲሱ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ያልተመዘገባችሁት የማኅበራችን አባላትም ሆናችሁ ያልተመዘገባችሁት መላው ሥራ ተቋራጮች ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በማንኛውም የመንግሥታዊ ግዥ ሥርዓት ውስጥ ተሳታፊ መሆን የሚችሉት በአዲሱ የኤሌክትሮኒክ የግዥ ሥርዓት ውስጥ የታቀፉ ሥራ ተቋራጮች ብቻ መሆናቸውን ከወዲሁ ተገንዝባችሁ በመርኃ-ግብሩ ላይ ተሳታፊ እንድትሆኑ አጥብቀን እንመክራለን፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር






Reviews
There are no reviews yet.