Conmart App

በቅዝቃዜ ወቅት ሲሚንቶ እንዳይበላሽ እና ጥራቱን እንዲጠብቅ ምን ማድረግ አለብዎት?

በዝቅተኛ ሙቀት (ቅዝቃዜ) ወቅት ሲሚንቶ እንዴት ይቦካል?

በቅዝቃዜ ወቅት ሲሚንቶ እንዳይበላሽ እና ጥራቱን እንዲጠብቅ ምን ማድረግ አለብዎት?

ወቅቱ የቅዝቃዜና የዝናብ ወቅት ሲሆን፣ የግንባታ ስራዎችን በብቃት ለመምራት የሲሚንቶ አዘገጃጀት ትክክለኛ መሆን አለበት። ዝቅተኛ ሙቀት የሲሚንቶውን የመድረቅ ሂደት በማዘግየት፣ ጥራቱን እንዲቀንስና የህንፃውን ጥንካሬ እንዲጎዳ ሊያደርግ ይችላል። ስለዚህ በቅዝቃዜ ወቅት ሲሚንቶ ሲቦክሉ ጥንቃቄ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ እንዲኖረዎት የሚከተሉትን ነጥቦች ይተግበሩ፦

• ለሲሚንቶ ቅልቅል ለብ ያለ ውሃ መጠቀም (በጣም ሞቃት እንዳይሆን ጥንቃቄ ያድርጉ)።
• ሲሚንቶው እንዳይርጠብና እንዳይበላሽ በደረቅና ከእርጥበት የጸዳ ቦታ ማስቀመጥ።
• በቅዝቃዜ ወቅት የሚቦከለውን የሲሚንቶ መጠን መቀነስ (አይደርቅም ብለው ብዙ እንዳይበክሉ)።
• የቦካውን ሲሚንቶ ከቅዝቃዜና ከእርጥበት ለመከላከል በፕላስቲክ መሸፈን።

ጥራት ያላቸውን የግንባታ ዕቃዎች በታማኝነትና በቅናሽ ዋጋ ለማግኘት ኮንማሬትን ይምረጡ። ለስራዎ አስተማማኝ አጋር ለመሆን ሁልጊዜ ዝግጁ ነን!

ስልክ፦ 0911283651, 0911283671
ድረ-ገጽ፦ conmaret.com

Conmaret የግንባታ ምርቶችን በሙሉ ለማየት እዚህ ይጎብኙ

በጥራትና በዋጋ እኛን የሚቀድም የለም፤ ይህ አቅርቦት እና ጥራት እኛ ጋር ብቻ የሚገኝ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *