Conmart App

ለቤትዎ የቧንቧ ዝርጋታ ትክክለኛውን ማቴሪያል መምረጥ ይፈልጋሉ? PPR ወይስ PVC?

ለቤትዎ የቧንቧ ዝርጋታ ትክክለኛውን ማቴሪያል መምረጥ ይፈልጋሉ? PPR ወይስ PVC?

ቤት ሲገነቡ የቧንቧ ዝርጋታ ትክክለኛ ምርጫ ማድረግ ለረጅም ጊዜ መቆየትና ለወደፊት የሚመጡ የጥገና ወጪዎችን ለመቀነስ ወሳኝ ነው። ብዙ ጊዜ በPPR እና በPVC ቧንቧዎች መካከል ያለውን ልዩነት በትክክል ባለማወቅ ስህተት መሥራት ለከፍተኛ የውሃ መፍሰስ እና ለከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ ይዳርጋል።

የሁለቱን ዋና ዋና ልዩነቶች እነሆ፦

• PPR ቧንቧዎች፦ ለሙቅ እና ለቀዝቃዛ ውሃ ተስማሚ፣ በሙቀት አማካኝነት በጠንካራ ሁኔታ የሚጣበቁና ለረጅም ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ፣ ለቤት ውስጥ ዋና የውሃ መስመር ተመራጭ ናቸው።
• PVC ቧንቧዎች፦ ለቀዝቃዛ ውሃ ብቻ የሚያገለግሉ፣ ለፍሳሽ ማስወገጃ እና ለዝናብ ውሃ ዝርጋታ ተመራጭ፣ በዋጋ ዝቅተኛ ቢሆንም ለሙቀት ውሃ የማይቋቋሙ ናቸው።

በኮምማሬት (Conmaret) ሁሉንም አይነት ጥራት ያላቸውን የPPR እና የPVC ቧንቧዎችን እንዲሁም ተያያዥ መለዋወጫዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ አቅርበን ይጠብቁዎታል። የትኛውን መምረጥ እንዳለብዎ ግራ ከገባዎት ባለሙያዎቻችንን በማማከር ትክክለኛውን ምርት እንዲወስዱ እናግዝዎታለን።

አድራሻ፦ ተክለሃይማኖት፣ ዊንጌት እና መርካቶ
ስልክ፦ 0911283651
ድረ-ገጽ፦ conmaret.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *