የምርት ሰርተፍኬሽን / PRODUCT CERTIFICATION

Request current price

Find የምርት ሰርተፍኬሽን / PRODUCT CERTIFICATION on Conmaret with supplier details for product availability, pricing, and ordering support.

  ጥያቄ ካለዎት እዚህ ይጠይቁ
Category:
Description

የምርት ሰርተፍኬሽን / PRODUCT CERTIFICATION
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት (ኢተምድ) በISO/IEC 17065 መሰረት እውቅና ያለው የምርት ሰርተፍኬሽን አገልግሎት እየሠጠ ይገኛል፡፡
የምርት ሰርተፍኬሽን ማለት ምርቶች የተጠቀሱ ተፈላጊ/ተጠባቂ መስፈርቶችን ማሟላታቸውን ለማሳየት በገለልተኛ ወገን የሚሰጥ የምርት ጥራት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ነው፡፡
የምርት ሰርተፍኬሽን አሰጣጥ ሂደት
1) ደንበኞች የአገልግሎት ጥያቄያቸውን በደብዳቤ ማመልከቻ ለድርጅቱ የሰርተፍኬሽን ክፍል ያቀርባሉ፡፡
2) ማመልከቻቸው ተገምግሞ ተቀባይነት ካገኘ፤ ፋብሪካው / ድርጅቱ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ኦዲት ይካሄዳል፡፡ በተጨማሪም ከምርት ሂደቱ ላይ ለላብራቶር ምርመራ የሚሆን ወካይ ናሙና ይወሰዳል፡፡
3) የፋብሪካው የመጀመሪያ ደረጃ ኦዲት ሪፖርት እና የፍተሻ ውጤት ግምገማ ይካሄዳል፡፡
4) የግምገማው ውጤት ምርቱ መስፈርቶች መሟላቱን የሚያረጋግጥ ከሆነ የደረጃ ምልክት እንዲጠቀም ይፈቀድለታል፡፡
5) በኦዲት ወቅት የታዩ የጥራት ጉድለቶች ካሉ ለድርጅቱ በጊዜ ገደብ የማስተካካያ እርምጃ እንዲወስድ በደብዳቤ ይገለጽለታል፡፡
6) የደረጃ ምልክት የመጠቀም ፈቃድ ከተሰጠው በኃላ የጥራት ሁኔታውን የጠበቀ ምርት እየተመረተ ስለመሆኑ ድርጅቱ ላይ የክትትል ኦዲት ይካሄድበታል፡፡
7) በኦዲት ወቅት ወሳኝ የጥራት ጉድለቶች በተደጋጋሚ ከታዩበት ፈቃዱን የማገድ እና የመሰረዝ እርምጃዎች በተከታታይ ይወሰዳሉ፡፡

Reviews (0)

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “የምርት ሰርተፍኬሽን / PRODUCT CERTIFICATION”

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Shipping & Delivery
More Offers
No more offers for this product!
Store Policies
Inquiries

General Inquiries

There are no inquiries yet.