Conmart App

የፕሮጀክትዎን ስኬት የሚያረጋግጠው የቴክኖሎጂ ውጤት – ቢም (BIM)!

ቢም (BIM) ምንድን ነው? ለምንስ ያስፈልጋል?

የፕሮጀክትዎን ስኬት የሚያረጋግጠው የቴክኖሎጂ ውጤት – ቢም (BIM)!

ቢም (BIM) ማለት የህንፃ ግንባታን ሂደት ከመጀመሪያው ንድፍ ጀምሮ እስከ ማጠናቀቂያው ድረስ በዲጂታል መንገድ በዝርዝር መረጃዎችን አቀናጅቶ የሚያቀርብ ዘመናዊ የሥራ ሂደት ነው። ይህ ቴክኖሎጂ የህንፃውን ባለ ሶስት አቅሳር (3D) ምስል ብቻ ሳይሆን፣ ስለ ግንባታው ግብዓቶች፣ ወጪ እና ጥራት ጠቃሚ መረጃዎችን በዝርዝር ይይዛል።

የቢም (BIM) አጠቃቀም በግንባታ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስህተቶችን ቀድሞ ለመለየት፣ የጊዜ እና የሃብት ብክነትን ለመቀነስ እንዲሁም የፕሮጀክቱን ጥራት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። በዘመናዊ ግንባታ ዓለም ውስጥ ውጤታማ ለመሆን ይህንን ቴክኖሎጂ መተግበር ለፕሮጀክቶች ስኬት እጅግ አስፈላጊ ነው።

የቢም (BIM) ዋና ጥቅሞች፦
• የግንባታ ስህተቶችንና የዲዛይን ግጭቶችን አስቀድሞ መለየት
• የቁሳቁስና የሰው ኃይል ብክነትን መቀነስ
• የፕሮጀክት ወጪንና ጊዜን በአግባቡ መቆጣጠር
• በባለሙያዎች መካከል የተሻለ የሥራ ቅንጅት መፍጠር

ለማንኛውም የግንባታ መረጃና የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የግንባታ ዕቃዎችን ለማግኘት ኮንማሬትን (Conmaret) ይዘው።

ለበለጠ መረጃ ይደውሉልን፦
የስልክ ቁጥር፦ 0911283651፣ 0911283671
ድረ-ገጽ፦ conmaret.com

Conmaret የግንባታ ምርቶችን በሙሉ ለማየት እዚህ ይጎብኙ

በጥራትና በዋጋ እኛን የሚቀድም የለም፤ ይህ አቅርቦት እና ጥራት እኛ ጋር ብቻ የሚገኝ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *